Wednesday, September 18, 2013

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች በከተማዋ ዙሪያ ከሚገኙ ገጠር የመጡ ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳይመዘግቡ የወረዳው መስተዳድር መመሪያ መስጠቱን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሸራሮ ከተማ የሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች በአከባቢው ከሚገኙ ገጠር  የሚመጡ ተማሪዎችን ተቀብለው እንዳይመዘግቡ የወረዳው መስተዳድር ጥብቅ መመሪያ አስተላልፋል። መስተዳድሩ እንዲህ ያለውን ትእዛዝ ወደታች ለማውረድ የተገደደው ከገጠር የሚመጡ ተማሪዎች ክትህዴን ጋር ስለሚገናኙ ኢንፎርሜሽን በማቀበል ሆነ ስለ ትህዴን አጠቃላይ ሁኔታ በት/ቤት ሊያስፋፉ ይችላሉ ከሚል ስጋት መሆኑን ቷውቋል።
የሸራሮ ከተማ ህዝብ ፤ ከገጠር የሚመጡ ተማሪዎች በአከባብያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩና አማራጭ ስላጡ ብቻ ትምህርት ፍለጋ ወደ ከተማዋ ለመምጣት እንደሚገደዱ ገልጸው በወረዳው መስተዳድር የተወሰደውን የተማሪዎችን የመማር መብት የማገድ እርምጃ አሳፋሪ ሲሉ ድርጊቱን አውግዘውታል።