በደረሰን ዘገባ መሰረት በምዕራብ ጎጃም የሚገኙ የፖሊስ አዛዦች በድንገት የተጠራ አሸካይ ስብሰባ ጥቅምት14,2005
ዓ/ም ያካሄዱ ሲሆን አሸካይ ስብሰባው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት በውል ባይታወቅም በአከባቢው የኢህአዴግ ስርዓትን በመቃወም የሚደረጉና
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ተቃውሞ ከወዲሁ በተቀናጀ መልኩ ለመቆጣጠር ሊሆን እንደሚችል በአከባቢው እየተድረጉ ካሉት እንቅስቃሴ
መረዳት ይቻላል፣
ይህ በእንዲህ እያለ የባህርዳር ጨርቃጭርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች ያቀረቡትን የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ በሚመለከተው
አካል አወንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ጥቅምት 15,2006 ዓ/ም ጥያቄያቸውን በማጠናከር መቀጠላቸውን ቷውቋል፣
ሰራተኞቹ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ እንዲያስነሱ ያስገደዳቸው ምክንያት እየተከፈላቸው ያለው ደሞዝ ካለው የኑሮ
ውድነት በመንግስት የሚቀርቡ የተለያዩ መዋጨዎችን ተደምረውበት ኑራቸውን በግባቡ መምራት ባለመቻላቸው ነው፣