Wednesday, October 30, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ተቃዋሚዎች ሰርገው ገብተዋል በሚል የከተማዋን ኗሪ ህዝብ ለመቀስቀስ በዞን መስተዳድር የተጠራው ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ፣




የሰሜን ምዕራብ ዞን የመስተዳድር አካላት በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ተቃዋሚዎች ሰርገው ገብተዋል በሚል የከተማዋን ኗሪ ህዝብ ለመቀስቀስ በጀመሩበት ጊዜ በስብሰባው የተገኙ ነባር የህወሓት ታጋዮች በኢህአዴግ ስርዓት በኢህአዴግ ስርዓት በአገሪቱና ህዝቦቻ ላይ እየተፈጸመ ያለ ግፍ በዝርዝር በማቅረብ በመቃወማቸው ካድሬዎች ይዘውት የመጡትን አጀንዳ ሳያቀርቡ ስብሰባውን ጥለው መውጣታቸውን ቷውቋል፣
ነባር ታጋዮቹ በስብሰባው ካቀረቡት የተቃውሞ ሃሳቦች መካከል የታገልንለትን ህዝባዊ ዓላማ ወደ ጎን በመተው ከህብረተሰቡ ይልቅ ግላዊ ጥቅማችሁን ታስቀድማላችሁ ፤ መኖሪያ ቤቶች በማን አለብኝነት በማፈራረስ ዜጎች አውላላ ሜዳ ላይ እንዲወድቁ አድርጓችሃል ፤ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ አፈና ይደረጋል የሚሉ ይገኙብታል፣