Sunday, October 6, 2013

የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ለመጠየቅ የሄዱት የአንድነት-ቅንጅት አመራር አቶ ካሳሁን ፈቃድ ለመጠየቅ የያዙትን ደብዳቤ ተነጥቀው እስር ቤት እንዲገቡ ተደረገ፣



የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም በአ/አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ እሚመለከተው የመንግስት አካል የሄዱት የአንድነት-ቅንጅት አመራር አቶ ካሳሁን ይልማ ከጉንበት-7 ግንኝነት አለህ በሚል ምክንያት በእጃቸው ይዘውት የነበረውን የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ መጠየቂያ ደብዳቤ ተቀምተው በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው መታሰራቸውን ቷውቋል፣
በአገሪቱ እየተካሄደ ባለው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ስጋት ውስጥ የገባው የኢህአዴግ ስርዓት የህዝቡን ጥያቄ ይዘው የተነሱትን የተቃዋሚ ሃይሎች አመራሮችን በጥላቻ አይን በማየት ከአሸባሪዎች ጋር ግንኝነት አላቸው በሚል የፈጠራ ክስ በየእስር ቤቱ ታጉረው እየተሰቃዩ ማድረግ የስርዓቱ መለያ መሆኑ የሚታወቅ ነው፣