Sunday, October 6, 2013

በአማራ ክልል ፤በዋግ ህምራ ዞን በሙስና የተጨማለቀና በኗሪው ህዝብ ላይ በደል ሲፈጽም የነበረ አንድ ካድሬ አቃቢ ህግ ላይ ህዝብ እርምጃ ወሰደ፣



በዋግ ህምራ ዞን በአቃቢ ህግ ሞያ ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ የነበረ የኢህአዴግ ካድሬ ህግን በመርገጥ በጉቦና በወገን በመስራት በአከባቢው ህዝብ ላይ በደል ሲፈጸም የነበረ አቶ ተስፋአለም መስከረም 17,2006 ዓ/ም በተተኮሰበት ጥይት ተመትቶ ህይወቱን ማጣቱን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ህዝብ በተለያዩ ክልሎች በኗሪው ህዝብ ላይ ግፍና በደል ሲፈጸሙ በነበሩ የጸረ-ህዝቡ ስርዓት ላይ እርምጃ ሲወስድ እንደቆየ የሚታወቅ ነው፣
ይህ በእንዲህ እያለ መስከረም 12,2006 ዓ/ም በአባይ ግድብ አንድ ፒክ አፕ መኪና ከምሽቱ 5።30 በጸረ-ተሽከርካሪ ፈንጅ ተመትቶ መቃጠሉን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣