የጋንታ አፈሹም አስተዳዳሪ አቶ ኪዱ ገብረጻድቅ በወረዳዋ ስር ላለች አንዲት ደካማ ጣብያ ከጣብያዋ አስተዳዳሪ
በመመሳጠር በወረዳው ሞዴል እንደሆነች አስመስለው በማቅረብ ከወረዳዋ በጀት ጣብያዋ 15 ሽህ ብር እንድትሸለም በማድረግ ሽልማቱ
የጣቢያዋና የወረዳው አስተዳዳሪ ተካፍለው እንደተጠቀሙበት ቷውቋል ፣
በድርጊቱ የተቆጣ የወረዳዋ ህዝብ ባለስልጣናቱ ተይዘው ወደ ህግ እንዲቀርቡ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን አቃቢ
ህግና ፤ ዳኞች ከባለስልጣናቱ ጎን በመቆም ክሱን ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣