Wednesday, October 30, 2013

የእግሪ ሓሪባና እምባ ፈቓዳ ኗሪዎች ከመሃከላችን በመረጥናቸው ሰዎች ካልሆነ ከላይ ከመንግስት በሚላኩብን ካድሬዎች አንመራም አሉ፣




በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን፤ በእንደርታ ወረዳ ፤የእግሪ ሓሬባና የእምባ ፈቛዳ ኗሪዎች ባለፈው ዓመት 2005 ዓ/ም በዞንና በወረዳ የመስተዳድር አካላት የደረሰባቸውን በደል እንዲታረም በተደጋጋሚ ጠይቀው መፍትሄ ስላልተሰጣቸው ከዛ ጊዜ ጀምሮ እምንተዳደረው ከመሃከላችን በመረጥነው ሰው ነው፥ ከእንግዲህ ከላይ የሚላክብን ባለስልጣን አንቀበልም በማለት በመቃወማቸው ሁሉንም የመንግስት አገልግሎት እንዳያገኙ ታግደዋል፣
የአከባቢው ኗሪዎች በመረጧቸው ሰዎች በመተዳደራቸው ደስተኞች ቢሆኑም ሁሉንም የመንግስት አገልግሎት ስለታገዱና ባለሃብቶችም ት/ቤት ፤ ፋርማሲ የመሳሰሉት ተቋማት በአከባቢው እንዳይከፍቱ ስለተከለከሉ ኗሪው በተለይም ህጻናትና እናቶች የህክምና አገልግሎት ለማግኘት እስከ መቐለ ከተማ ድረስ በእግር ለመሄድ ስለሚገደዱ መንገድ ላይ ለከፋ ስቃይና አንዳንዶችም ይወታቸውን ያጡ እንዳሉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ተማሪዎች እስከ ዂሓ ድረስ በመሄድ ቤት ተከራይተው ለመማር የተገደዱ ሲሆን አቅሙ የሌላቸው ደግሞ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን ቷውቃል፣