Sunday, October 6, 2013

በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ስራ ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ የውጭ ባለሃብቶች መንግስት በጫነባቸው ከፍተኛ ግብር ተማረው ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ በመውጣት ላይ ናቸው፣



በባህርዳር ከተማ የምግብ ዜይት ፋብሪካ አቋቁመው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ሱዳናዊያን ባለሃብቶች መንግስት የጫነባቸውን በጥናት ያልተደገፈ ከፍተኛ ግብር ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠንና በጣም ጎጂ ሆኖ ስላገኙት የተጠየቁትን ግብር ንብረታቸውን ሸጠው በመክፈል በያዝነው ወር ኢትዮጵያን ለቀው ወደ ሱዳን መመለሳቸውን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በድርጅቱ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ በካታ ወገኖች ስራ በማቆማቸው ምክንያት እራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩበት ገቢ አጥተው በከባድ ችግር ላይ ይገኛሉ ፣ ህይወታቸውን እስከ ማጥፋት የደረሱ እንዳሉም የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣