እስረኞቹ በፍኖተ ሰላም ከሚገኘው እስር ቤት ወጥተው የጉልበት ስራ ወደ እሚሰሩበት አከባቢ በመጓዝ ላይ
የነበሩ ሲሆን ቁጥራቸው ከ 1500 በላይ ይሆናል፣ ወደ ባህርዳር ከተማ ሲያመራ የነበረ አንድ ከባድ ተሽከርካሪ 01 ቀበሌ አከባቢ
ሲደርስ በእግር ሲጓዙ በነበሩት እስረኞች ላይ ድንገት ባደረሰው አደጋ ሦስት እስረኞች ወዲያውኑ ሲሞቱ ቁጥራቸው ለግዜው ባልታወቁ
ሌሎች ቆስለዋል፣ አደጋው የደረሰው ጥቅምት 30,2006 ዓ/ም መሆኑ ቷውቋል፣
እንዲሁም ከዘኑ ሳንወጣ በዳሞት ወረዳ ከሚገኙ 33 ቀበሌዎች የተውጣጡ ቁጥራቸው 330 የሚሆኑ ገበሬዎች
የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በሚል ከጥቅምት 15 እስከ ሕዳር 8,2006 ዓ/ም በፍኖተ ሰላም ከተማ ስብሰባ አካሄዱ፣ ስብሰባው
የተመራው በወረዳው ም/ቤት አስተዳደር አቶ አበበ ውቤ ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ ወቅቱ የመኸር ወቅት ነው ፥ ብዙ የደከምንበት አዝመራ
ገና ከማሳው አልተነሳምና እርባና በሌለው ስብሰባ ጊዜአችንን አታባክኑብን በቃን በማለት በመቃወማቸው የታሰበው ውጤት ሳያመጣ መጠናቀቁን
ቷውቋል፣