Saturday, November 23, 2013

አገራዊ ስሜትና አስተሳሰብ የሌለው ስርአት ለህዝብ ጥብቅና ሊቆም አይችልም!!

የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ተከታታይ አመታት በጫንቃው ላይ ሆነው ሲገዙት በነበሩት ገዥዋች ምክንያት ኑሮው ከቀን ወደ ቀን ተጎሳቁሎ ወደ ከፋ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ችግሮች ከገባ አያሌ  ዘመናት አስቆጥረዋል፣
watch more by TPDMTV AMHARIC
የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናትና ካድሬዎች የህዝቡን ሰብኣዊና ዴሞክራሲያዊ መብት እንዴት መከበር እንዳለበት በአተረጓጎሙና ሃሳቡን በማቀነባበር በኩል ከማንም በላይ አብራርተውና አጉልተው ቢገልፁትም። ወደ ህዝቡ ወርደው ሲሰሩበትና ሲተገቡሩት ግን። የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት ለማስከበር ሲሉ ፍፁም አይተገብርቱም ቢባል በትክክል ሊገልፃቸው የሚችል ሃቅ ነው፣
      ህዝባችን እንደ ዜጋ በሀገሩ ሰርቶ እንዲኖር፤ ሰላም አግኝቶ ማህበራዊ ኑሮውን እንዲመራ፤ በዓይነ ቁርኛ ሳይተያይ በቋንቋና በብሄር ሳይለያይ አገራዊ ስሜቱንና አቅሙን አስተባብሮ ሃገራዊ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እንዲያበለፅግና፤ በአንድ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ተደራጅቶ። ፍላጎቱንና አላማውን ከግብ ሊያደርስ ያልቻለው። ዴሞክራሲያዊ መብቱ ስለ ተነጠቀ ብቻ ሳይሆን። እንደ ህዝብ ሰብኣዊ ክብሩ ተነፍጎ። ተኝቶ የምያድርባት መኖርያ ቤት፤ የሚበላው ዳቦና የሚለብሰው ጨርቅ አጥቶ። በአገሪቱ ባለው ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ ቀውስና  ብልሹ አስተዳደር ምክንያት በየአመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወደ ተለያዩ ባእድ አገሮች መሰደዱ የሚያሳዝን ነው፣
      ይህንን ሁኔታ የሚያመለክተን ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግ ካድሬዎች እንደሚሉት የህዝባችን የኑሮ እድገት እንደጨመረ፤ የአገራችን ምጣኔ ሃብት ሰማይ እንደደረሰ የሚያሳየን ሳይሆን። በተገላቢጦሽ የህዝቡን ድህነት  ከነበረበት በባሰ መልኩ እንዳሽቆለቆለና አንዳችም የሃብትና የብልፅግና እመርታ እንዳላሳየ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተደበቀ አይደለም።
     በስደት ላይ ባሉ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ያለ ግፍ ካለፉት አመታት በከፋ መልኩ እየተባባሰ መጥቷል ፣በተለይም በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ በስደተኛ ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ዘግናኝ ግፍ እጅግ ልብን የሚሰብር ነው፣ ይህ አይነቱ ግፍ በተለያዩ የአረብ አገሮችም በዜጎቻችን ላይ ሲከሰት የቆየ የመብት ጥሰት ተቀጥያ መሆኑንና አገራችን እየገዛ ያለው አምባገነን ፀረ ህዝብ ስርአት ምክንያት መሆኑን። ለማንኛውም ህሊና ያለውና አርቆ አስተዋይ ወገን ድብቅ  አይደለም፣   
       በስልጣን ላይ ባለው የኢህአዴግ ገዢ መንግስት በፈጠረው ብልሹ አሰራር፤ አድልዎና ፖለቲካዊ ቀውስ በአገሩ ሰርቶ ለመኖር ባለመቻሉ ኑሮውን ለማሻሻልና ለመለወጥ፤ በድህነት እየተሰቃዩ ያሉ ቤተሶበቹና ወገኖቹ እረዳሎህ ከሚል በጎ አስተሳሰብ ብቻ ተነሳስቶ። አስከፊ በራሃዎች፤ ምድረ-በዳዎችና ውቅያኖሶችን አቋርጦ እንደ እድል ከሞት ተርፎ ወዳሰበው ቦታ የደረሰው ስደተኛ ወገን። ገና ከቀዩና ከሃገሩ ሳይወጣ  ሲያስበው የነበረ  ሳይሳካለት ቀርቶ ለበርካታ አመታት ላቡን አንጠፍጥፎና ደክሞ  የሰበሰበው ገንዘብና ንብረት በዎርቦሎች ተነጥቆ ሲያበቃ ድብደባ፤ እስራት፤ በተለይ ደግሞ ሴት እህቶቻችን ከቤቶቻቸውና ከየጎደናው እየታፈሱ የወሲብ አመፅና እስከ ሞት የደረሰ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየተፈፀመባቸው ይገኛሉ።
   የሚገርመው! ይህንን እስከፊና አርቆ አሳቢነት በጎደሎው መንገድ። በሳውዲ መንግስት ባለስልጣናትና ወመኔዎች። በወገኖቻችን ላይ የተፈፀመውና እየተፈፀመ  የለው አስክፊ ድርጊት። የአለም የስደተኞች መብትና ህግ የጣሰ ነው በሚል ምክንያት። በተለያዩ ክፍላተ አለሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተግባሩን በመቃወም። በሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፅሕፈት ቤቶችና ትላልቅ የመሰብሰብያ ቦታዎች ተገኝተው ሃቀኛና ወገናዊ ተቃውማቸውን ሲገልፁ።  የኢህአዴግ ባለስልጣንት ግን በበኩላቸው ለማስመሰልና ለህዝቦቻቸው አሳቢና ተቆርቋሪ ሆነው በመቅረብ። ዛሬም እንደ ትላንቱ አንዳችም አገራዊ ስሜትና አስተሳሰብ በሌለው እንካ ስላንትያ ተዘፍቀው።  በላዩ ላይ ግፍ እየተፈፀመበት ላለው ስደተኛው ወገናችን ጠበቆች ለመምሰል። እያካሄዱት ያለው ጩኸትና መቅበዝበዝ። ለኢትዮጵያ ህዝብና ለአለም ማህበረሰብ የሚያሳስብ ጉዳይ ሁኗል፣
      ምክንያቱም ወያኔዎች ህዝቡን በማታለል የስልጣን እድሜያቸው  ለማራዘም ካልሆነ የችግሩ ምንጭና የህዝቡን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው ማለቅያ የሌለው ፍልሰት እንዴት ማስወገድ ይቻላል የሚለውን መላምት በማግበስበስ ከሳውዲ ልኡላዊያን ጋር በማበር ለም መሬታችን በመስጠት በህዝባችን ላይ ዘመናዊ ባርነት በማካየድ ላይ መቆየታችውና አሁንም በተለያዩ ዜዴዎች በመቀጠል ላይ ናቸው። ስለሆነም ህዝባችን መሪ ሹም እንዳጣ ንብ ከመበታተኑ በፌት። በአገሩ መሬትና  ከቦታው ሳይፈናቀል  አገሩ ውስጥ ስራ አግኝቶ በሰላም ሰርቶ በነፃነት ኑሮውን መግፋት ይችል ዘንድ የኢህአዴግ ገዢ መንግስት በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ንቅናቄና ትግል ከስልጣኑ መገርሰስ ይኖርበታል፣  
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!