Tuesday, November 19, 2013

በትግራይ ክልል በገጠር የሚኖረው አርሶ አደር ህብረተሰብ በማዳበሪያ እዳና በማህበራዊ አገልግሎት እጦት ምክንያት ችግር ላይ መውደቁን በቅርቡ ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል የተቀላቀሉ ወጣቶች ገለጹ፣




ወጣቶቹ በገጠር በእርሻ ስራ የሚተዳደረው አርሶ አደር ካለፍላጎቱ በውድ ዋጋ ማዳበሪያ እንዲወስድ በመንግስት እንደሚገደድና በተለያዩ ተፈጥራዊ ችግሮች ምክንያት ገበሬው ምርታማ ሳይሆን ቀርቶ የተበደረውን የማዳበሪያ ዋጋ በውቅቱ መክፈል በማይችልበት ሁኔታ ካመጣህ አምጣ እየተባለ በስርዓቱ ካድሬዎች የተለያዩ በደሎች እንደሚደርስበት ገልጸዋል፣
ህዝባዊ ማህበራዊ አገልግሎት በተመለከተም በጣም የተዳከመ እንደሆነ የገለጹት ወጣቶቹ በርካታ ወገኖች በተለይም እናቶችና ህጻናት የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ማእከል በአቅራቢያቸው ባለመኖሩና መድሃኒት ፍለጋ ብዙ ሰዓታት ለመጓዝ ስለምገደዱ በወባ በሽታ ሳይቀር ለስቃይና ሞት ይዳረጋሉ፣
ወጣቶቹ አያይዘው በትምህርትም ቢሆን እድሚያቸው ለትምህርት የደረሰ ህጽናት ት/ቤቶች በአቅራቢያቸው ስላልተገነቡ የመማሩ እድል ማግኘት አልቻሉም፣ ስንቅ በመያዝ ራቅ ወዳለ ቦታ በመሄድ ለመማር የሚሞኩርቱም ቢሆን የመማሩ እድል የሚያገኙት የመግቢያ ፈተና ከወሰዱ ብሁውላ ነው ቢባልም አብዛኛው ተማሪ እድሉ የሚያገኘው በእውቀቱ ተመዝኖ ሳይሆን በጥቅማ ጥቅም ነው በማለት ሁኔታው ገልጸውታል፣
በተለይም ወጣቱ ገ/ሃዋሪያና ሓድሽ ጸጋይ ወጣቱ ለስርዓቱ ካድሬዎች እየተገደደ ወደ ውትድርና ማሰልጠኛ ማእከላት እየተወሰደ መሆኑን ጠቅሶ አብዛኛው ወጣት ከማሰልጠኛ ማእከላት እየጠፋ ወደ ቀየው በመመለስ ላይ መሆኑን አስረድተዋል፣
ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ከተቀላቀሉት ወጣቶች መካከል።-
1-ገ/ጻድቅ ብርሃነ ምራጭ ፤ ማእከላዊ ዞን ፤ መረብ ለኸ ወረዳ ፤ ዓዲ-ሹምብሩህ ጣብያ
2-ሃለቃ መሓሪ ጉዕሽና ገ/ሃዋርያ ገ/ስላሰ ከማእከላዊ ዞን ፤ አሕፈሮም ወረዳ ፤ ሰምሃል ጣብያ
3-ገ/ሃዋሪያ ሓድሽ ወ/ሚካኤል ፤ ከማእከላዊ ትግራይ ዞን ፤ መረብ ለኸ ወረዳ ፤ ሃፍተማሪያም ጣብያ
4-ግደይ ታደሰ ስዩም ፤ ከማእከላዊ ዞን ፤ ወርዒ ለኸ ወረዳ ፤ ማይኩሕሊ ጣብያ
5-ተኽላይ ጸጋይ ገብሩ ፤ ከማእከላዊ ትግራይ ፤ መረብ ለኸ ወረዳ ፤ ከደብረ ሓርማዝ ጣብያ ይገኙበታል፣