የሸራሮ ከተማ ነጋዴዎች ግብር የከፈልንበት ህጋዊ ደረሰኝ በእጃችን እያለ ዳግም ሌላ ተጨማሪ ግብር እንድንከፍል
በስርዓቱ ካድሬዎች እየተደረገብን ያለው ጫና አግባብነት የሌለው መሆኑን ቷውቆ ህጋዊ መፍትሄ ይሰጠን በማለት በአንድ ድምጽ በመጠየቅ
ላይ ናቸው፣
ኗሪነታቸው በከተማዋ ከሆኑት ነጋዴዎች መካከል አቶ ይርጋለም የተባለ ዜጋ ግብር መክፈሉን የሚያረጋግጥ ህጋዊ
ደረሰኝ በእጁ እያለው ሌላ ተጫማሪ ግብር መክፈል አለብህ በሚል ህገ-ወጥ አሰራር በንግድ ስራ ያሰማራውን የጭነት መኪናው በቁጥጥር
ስር እንዲውል ተደርጓል፣
በሁኔታው ቅር የተሰኘው የከተማዋ ኗሪ ህዝብ የወረዳው አስተዳዳሪ ወዲ-አወጣሽ ከስልጣኑ ይነሳ የሚል ከባድ
ተቃውሞ አስነስቷል፣ የዞን አስተዳዳሪ አቶ ጎይቶኦም ይብራህና የጸጥታ ሃላፊ አቶ ጥላሁን በሪሁን ሁኔታውን ለማርገብ እቦታው ተገኝተው
ህዝቡን በመሰብሰብ ባነጋገሩበት ጊዜ ህዝቡ መጀመሪያ የወረዳው አስተዳዳሪ ከስልጣኑ ይነሳ በሚል አቋም በመጽናቱ ከክልል ተነጋግረን
ችግሩን ለመፍታት እንሞክራለን የሚል ምላሽ እንደሰጡዋቸው ለማወቅ ተችሏል፣