Wednesday, November 27, 2013

የኢህአዴግ ስርዓት የጸጥታ ሃይሎች በፍኖተ ሰላም ከተማ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ የታሰሩ እስረኞችን በመሰብሰብ፤ በመሃከላችሁ አሸባሪዎች አሉ አጋልጥዋቸው በማለት እንዳስፈሯሯቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



  በደረሰን ዘገባ መሰረት በፍኖተ ስለም ከተማ በሚገኝ አንድ እስርቤት ውስጥ ታጉረው የሚገኙ እስረኞች በመሰብሰብ   በመሃከላችሁ አሸባሪዎች እንዳሉ የደረስንበት ስለሆነ ከመንግስት ጋር በመተባበር አጋልጧቸው፣ ይህንን ሳታደርጉ ብትቀሩ ግን በናንተ ላይ ያለን አያያዝ ይቀየራል በማለት እስረኞቹ ከማንኛውም ሰው ጋር ከቤተሰቦቻቸውም ጭምር እንዳይገናኙ መታገዳቸውን ቷውቋል፣
   የእስረኞቹ ቤተሰቦች በየቀኑ ምግብ ይዘው እስረኞችን ለመጠየቅ በሚሄዱበት ጊዜም ምግብ የወሰዱበት ዕቃ ሆነ ቅያሪ ልብስ ይዘው ወደቤታቸው እንዲመለሱ እየተደረገ የቆየ ሲሆን በቅርቡ ግን ምግብ ይሁን ልብስ ለተረኛ ፖሊስ አስረክበው ከታሰሩት ቤተሰቦቻቸው ምንም መልስና መልእክት ሳያገኙ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው፣ በዚህም የእስረኞቹ ቤተሰቦች ከእስረኞቹ ጋር መገናኘት ስላልተፈቀደላቸው የእስረኞቹን ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፣