አስተማሪዎቹ ባደረጉት
ተቃውሞ የጥቅምት 2006 ዓ/ም ደሞዛቸው ሳይቆረጥ የታለፈ ቢሆንም ከህዳር 2006 ዓ/ም ጀምሮ ግን አስተማሪዎቹ ፈቃደኛ ቢሆኑም
ባይሆኑም መንግስት በራሱ ጊዜ የአስተማሪዎቹን ደምዎዝ መቁረጥ እንደሚጀምር ግልጽ አድርጓል።
ነገር ግን አስተማሪዎቹ መንግስት ደሞዛችንን በጉልበት የሚቆርጥብን ከሆነ ሳንበላ
መስራት ስለማንችል ማስተማርን አቁመን የተገኘውን ጊዚያዊ ስራም ቢሆን እየሰራን ህይወታችንን ለማቆየት እንገደዳለን በማለት ተቃውማቸውን
በማቅረባቸው ፤ በሁኔታው የተደናገጡ የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መለስ አድነውና የወረዳው የትምህርት ክፍል ሃላፊ አቶ ጴጥሮስ የተባሉ
የስርዓቱ ካድሬዎች በቅርቡ አስተማሪዎችን በመሰብሰብ ተቃውሞን በሚቀሰቅስ ማንኛውም አስተማሪ ላይ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ
ይወሰዳል በማለት እዳስፈሯሯቸው ቷውቋል፣
ከወረዳው ሳንወጣ የወረዳዋ መስተዳድር ማንኛውም የወረዳዋ ኗሪ ቤት ለምግዛትም
ሆነ ለመሸጥ ሲፈልግ ሦስት በመቶ(3%) ለመንግስት ገቢ እንዲያደርግ የሚያስገድድ መመሪያ አውጥቷል፣ መመሪያውን ተከትሎ የወረዳዋ ኗሪ ህዝብ ተቋውመውን እየገለጸ ቢሆንም የወረዳው
የመንግስት ባለስልጣናት ግን ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በህዝቡ ላይ በደል መፈጸም ሥራችን ብለው ተያይዘውታል፣