ነጋዴዎቹ ህጋዊ የንግድ
ፈቃድ ኖሯቸው በመቐለ ከተማ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶችን ከፍተው በንግድ ስራ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን
ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ማንኛውንም ንብረት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት የተገዛበትንና የሚሸጥበትን ዋጋ የሚያመለክት ሰነድ
ለሚመለከተው አካል ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው የሚያዝዝ መመሪያ
በከተማዋ አስተዳደር ወርዳል፣
መመሪያው ድንገት የመጣ ከመሆኑም በላይ አፈጻጸሙን በተመለከተ ግልጽ ያልሆነላቸው
አንዳንድ ነጋዴዎች በተለመደው መንገድ ሲሰሩ በመገኘታቸው ድርጅቶቻቸው እንዲታሸጉ መደረጉን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
የንግድ ድርጀቶቹን በማሸግ በመንግስት የተወሰደው እርምጃ ሃላፊነት የጎደለው
ነው በማለት ነጋዴዎቹ ተቃውማቸውን የገለጹ ሲሆን፥ ተቃውመውን ተከትሎ አቶ ምሉ ግደይና አቶ አብረሃ ሓጎስ የተባሉ ዜጎች የሚገኙባቸው
በርካታ ነጋዴዎች በቀበሌ 20 በተለምዶ ‘እንዳሚካኤል’ እየተባለ በሚጠራ ቦታ በሚገኝ እስርቤት ታስረው ይገኛሉ፣