Wednesday, November 27, 2013

የእንደርታ ወረዳ የመስተዳድር አካላት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት እንዲውል በሚል ከአከባቢው ህዝብ የተሰባሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው አዋሉት፣



   በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ፤ በእንደርታ ወረዳ ፤ የማይ-ጸዶ ጣብያ ኗሪዎች የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ ወረዳው ስላሰበ ስራውን ለመጀመር ይቻል ዘንድ ከህዝቡ ገንዘብ ይሰባሰብ የሚል ሃሳብ በወረዳዋ መስተዳድር ስለቀረበ በ 2004 ዓ/ም ከአንድ መቶ ሽህ ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ከህዝቡ በማሰባሰብ ለወረዳው አስረክበዋል፣ ነገር ግን እስካሁን ድረስ የተሰራ ስራም ሆነ የሚታይ እንቅስቃሴ የለም ሲሉ ኗሪዎቹ ያማርራሉ፣
   ኗሪዎቹ ከሁለት ዓመታት በላይ በትእግስት የጠበቁ ሲሆን በያዝነው ሳምንት ለጣብያው አስተዳዳሪ አቶ ጎይቶኦም ጉዳዩን አስመልክተው አግባባነት ባለው መንገድ ጥያቂያቸውን አቅርበዋል ፥ ሆኖም አስተዳዳሪው የኗሪዎቹን ጥያቄ በአግባቡ ማስተናገድ ስላልቻለ ተበዳዮቹ የወረዳው አስተዳደርና ተከታዮቹ በሙስና ተጨማልቀዋል ሊጠየቁ ይገባል በማለት ተቃውማቸውን በአደባባይ በመግለጽ ላይ መሆናቸዉን ታውቀዋል።