በአማራ ክልል የሰቆጣ ወረዳ ኗሪዎች በወረዳዋ አስተዳደር በተጠራ ስብሰባ መንግስት ከገቢያችን ጋር የማይመጣጠን
ከፍተኛ ግብር እንድንከፍል እያስገደደን ነው ሲሉ አማረዋል፣ ከነዋሪዎቹ መካከል ወ/ሮ ክሑሎ ባህታ የተጠየቁት ግብር 77 ሽህ ብር
ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ቢሆንም ለህይወታቸው በመስጋት የነበራቸው ንብረት ሸጠው ለመክፈል መገደዳቸውን ጠቅሰው አሁን ህይወታቸውን
መምራት በማይችሉበት ሁኔታ እንደሚገኙ አስረድተዋል፣
በስብሰባው የተገኙ የወረዳዋ ኗሪ ህዝብ መንግስት እየተከተለው ባለው የግብር አከፋፈልን ስርዓት ያጣና ዜጎችን
ወደ ድህነት የሚያስገባ በዝርፊያ የሚገለጽ ነው ሲሉ ገልጸውታል፣