Sunday, November 3, 2013

ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ገንዘብ ለመዝረፍ የሞከሩ የሑመራ ቅርንጫፍ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ፣




በሑመራ ከተማ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ተቀጥረው የሚሰሩ ስማቸው ለጊዜው ያልተጠቀሰ ሁለት ሰራተኞች ኗሪነታቸው በራውያን ከተማ ከሆኑና ከኢአዴግ ስርዓት ጋር የቅርብ ግንኝነት ካላቸው ሌሎች ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር በግለሰቦቹ ስምና አድራሻ ጥቅምት 17,2006 ዓ/ም ሁለት ሚልዮን ብር በሃዋላ አ/አበባ ወደሚገኘው ዋና የአዋሽ ባንክ እንዲላክ ከተደረገ ብሁዋላ ግለሰቦቹ አ/አበባ ሄደው በስማቸው የተላከላቸውን ብር አውጥተው እንዲከፋፈሉት ነበር ውጥናቸው ፥ ነገር ግን በመሃል ስለተነቃባቸው በአካባቢው ህዝብ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው በእስር ላይ ይገኛሉ፣
እንዲህ ዓይነቱ ተግባር በመላ ሃገሪቱ በተደጋጋሚ የሚታይ ሆኖ የህዝብንና የሃገርን ሃብት እየዘረፉ መጥፋት የኢህአዴግ ስርዓት የፈጠረው መወገዝ ያለበት አስጸያፊ ተግባር ነው ሰሉ የአከባቢው ኗሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፣