Sunday, November 3, 2013

የሸራሮ ከተማ ኗሪዎች መንግስት በሚጭንብን ከገቢያችን ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር ምክንያት ኑራችንን በአግባቡ መምራት አልቻልንም ይላሉ፣




ከጥቅምት 18,2006 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ ያለው የግብር አከፋፈል አሰራር የስራ እንቅስቃሴን በሚገባ ያልመረመረ ኗሪዎቹ ሰርተው ከሚያገኙት ገቢ በላይ ስለሚሆን አብዛኛው የከተማዋ ኗሪዎች ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ለመሰደድ እየተገደዱ ነው፣
ይህ በእንዲህ እያለ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ የሚገኙ የፖሊስ አባላት የደምብ ልብስ በወቅቱ ስለማይሰጣቸው ባለቀ ልብስና በነጠላ ጫማ ለመስራት ተገደዋል፣ የፖሊስ አባላቱ በህጉ መሰረት የደምብ ልብስ በአመት ሁለት ጊዜ የማይታደል ከሆነ ስራችን ለማቆም እንገደዳለን ሲሉ ይናገራሉ፣