Friday, November 1, 2013

በቋራ ወረዳ የሚገኙ የመስተዳድር አካላት ለልማት በሚል ሰበብ ከህዝብ የተሰባሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው አዋሉት፣




በቋራ ወረዳ የሚገኙ በየደረጃው ተመድበው የሚሰሩ የመስተዳድር አካላት ለልማት በሚል ሰበብ ከህዝብ የተሰባሰበውን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው አዋሉት፣ በተለይም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለም ቡሬ የተባለ ካድሬ ከህዝብ በተሰባሰበው ገንዘብ ለልማት የተገዙትን የህንጻ መሳሪያዎችን ስልጣኑን አለአግባብ በመጠቀም የግሉ መኖሪያ ቤት እንዳሰራበት ቷውቋል፣
አቶ አለም ቡሬ ከዘረፈው ንብረት የቤት ክዳን ቆርቆሩ ፤ ስሚንቶ ፤ ተንዲኖና ሌሎች የህንጻ መሳሪያዎች የሚገኙበትና በመቶ ሽዎች ብር የሚገመት ሲሆን ግለሰቡ ንብረቱን መዝረፉን ቷውቆ ጥቅምት 9,2006 ዓ/ም ወደ ፍርድ ቤት ቀርቦ በእስር እንዲቆይ ተደርጓል ፣ ነገር ግን በጉቦና ከዳኛው ጋር ባለው የግል ግንኝነት ምክንያት ከሦስት ቀናት ብሁዋላ መፈታቱን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
የህዝብ ገንዘብ በመዝረፍ ሲያላግጥ የቆየው አስተዳዳሪ ተብየው ከእስር ቤት እንደተለቀቀ ዳግም ክስ ሊመሰረትብኝ ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ከአከባቢው መሰወሩን ቷውቋል፣