በደረሰን ዘገባ መሰረት በማእከላዊ ዞን ፤ አክሱም ከተማ የሚገኘው የቅድስተ ማሪያም ሆስፒታል ለባለስልጣናትና
ቤተሰቦቻቸው በአግባቡ አገልግሎት ሲሰጥ በአንጻሩ ለአካል ጉዳተኞችና ለሰማእታት ቤተሰብን ግን በአግባቡ አያስተናግድም፣አካል ጉዳተኞቹንና
የሰማእታት ቤተሰቦችን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችላቸውን ወረቀት ይዘው ወደ ሆስፒታሉ በሚሄዱበት ጊዜ የምርመራ
አገልግሎት ብቻ በመስጠት የሚታዘዝላቸውን መድሃኒት ከውጭ ፋርማሲ ገዝተው እንዲጠቀሙ ስለሚደረግ በአቅም ማነስ ምክንያት የታዘዘላቸውን
መድሃኒት ገዝተው መጠቀም ስለማይችሉ ለስቃይና ሞት እየተዳረጉ ነው፣
የአካል ጉዳተኞቹና የሰማእታት ቤተሰቦች ነጻ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም በተጨባጭ
ግን የተሟላ የህክምና አገልግሎት አይሰጣቸውም ፣ አቶ አረጋይ የተባለ የህክምና አገልግሎትን ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ የሄደ አንድ
አካል ጉዳተኛ ከምርመራ ብሁዋላ የታዘዘለትን መድሃኒት በሆስፒታሉ እያለ የለም በሚል ከፋርማሲ ገዝቶ እንዲጠቀም ተነግሮታል፣ ነገር
ግን አካል ጉዳተኛው ገንዘብ ከፍለው በሆስፒታሉ ለሚታከሙ ሰዎች መዳኒቱ ሲሰጣቸው በማየቱ የታዘዘለትን መድሃኒት በእጅ አዙር መግዛቱን
ጠቅሶ በሆስፒታሉ የሚታየውን ኢፍትሃዊ አሰራር አጋልጧል፣