Sunday, October 6, 2013

የኢህአዴግና የካርቱም መንግስት የጸጥታ ሃይሎች በመተባበር የተቃዋሚ ድርጅቶች ትደግፋላችሁ በሚል ሰበብ በሱዳን በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ላይ አፈና እየፈጸሙ መሆኑን ከካርቱም የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት የኢህአዴግና የካርቱም መንግስት የደህንነት አካላት አንድ ላይ በመሆን ኢትዮጵያኢያን በሚኖሩበት አከባቢ ድረስ በመሄድ በየመኖሪያ ቤቱ በመግባትና በመፈተሽ የትህዴን አባላት ናችሁ በሚል ሰበብ የታፈኑ በርካታ ዜጎች እስካሁን ድረስ አድራሻቸው ለማወቅ አልተቻለም፣
ለብዙ ዓመታት በዜጎች ላይ በደል ሲፈጽም የቆየ ንጉሰ የተባለ የደህንነት አባል መሓመድ ከተባለ ባልደረባው ጋር በመሆን ከታፈኑት ሰዎች መካከል የማነ ፤ አሚን ፤ ገሬና ሌሎሎችም በርካታ ወገኖቻችን እንደሚገኙበት የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣