በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ
ዞን ሽሬ እንዳስላሴ ቀበሌ 01 ልዩ ስሙ ቄራ በተባለ አካባቢ። ኗሪዎቹ ለአመታት ሲጠቀሙበት የነበረ በቁጥር እስከ 80 የሚደርስ
መኖርያ ቤት እንደፈረሰና። በ02 ቀበሌ ማይ ኣድራሻ አካባቢም። በከተማው አስተዳደር ህጋዊ ፈቃድ አግኝተው ለተሰሩትና ህዝቡ ሲገለገልበት
ለቆየ መኖርያ ቤት። የሽሬ እንዳስላሴ ከንቲባ አቶ ሃይለ አዳነና የፖሊስ አዛዡ ገዛኢ በመሆን። ቤቱን የሚያፈርሱ ግብረሃይል በማደራጀት የህዝቡን የድረሱልን
ጭሆት ሳይበግራቸው በትእዛዝ አስገድደው እንዲፈርስ እንዳደረጉት። ተበዳዮቹ ካቀረቡት ቅሬታ ለማወቅ ተችለዋል፣
ማንኛውም ቅድመ ሁኔታና ማስጠንቀቅያ ሳይሰጣቸው ቤታቸው የፈረሰባቸው
እነዚህ ነዋሪዎች። ለፈረሰባቸው ቤት የተሰጣቸው ካሳና ተለዋጭ መሬት ባለመኖሩ። ባሁኑ ወቅት አራስ እናቶችና ህፃናቶች የሚገኙበት
በርከት ያሉ አባወራዎች። ምንም አይነት መጠለያ ባለማግኘታቸው አውላላ ሜዳ ላይ ተጥለው ለተለያዩ ባህርያዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች
ተጋልጠው እንዳሉ መርጃው አክሎ ያስረዳል፣