በደረሰን መረጃ መሰረት
የሰሜን ምእራብ ትግራይ ዞን ዋናው አስተዳዳሪ የነበረው ኣቶ ሚኬኤለ አብርሃና የዞኑ ፀጥታ ሃላፊ ኣቶ አዳነ አሰፋ አብሮው እየሰሩ የቆዩ ቢሆንም። በግላዊ ጥቅም የተነሳ በመሃከላቸው
ልዩነት ተፈጥሮ መቆየቱንና። አሁንም ለህዝብ ተብለው በመጡ የውሃ ፓምፕ ጀነሬተሮች ምክንያት። ራስ በራሳቸው ቢካሰሱም ሁኔታው ወደ
ሚመለከታቸው አካላት ቀርበው ህጋዊ መፍትሄ ሊደረግለት እንዳልተቻለ ለማወቅ ተችለዋል፣
በስርአቱ ውስጥ በሚገኙ የበላይ አመራሮች። በግላዊ ጥቅም ተነሳስተው
ራስ በራሳቸው መናቆርና መካሰስ የተለመደ ቢሆንም። ወደ ሚመለከታቸው አካል ቀርበው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኙ ከማድረግ አንፃርና።
እያስተዳደሩት ላለ ህዝብ ያላቸው ውስጣዊ አሰራር ግልፅ በማድረግ ሂደት ድፍረትና ተነሳሽነት ስላልነበራቸው። አሁንም ለነዚህ የዞኑ
የበላይ አመራሮች ግልፅ ባልሆነ ስውር አሰራራቸው ተጠቅመው። ለአቶ ሚኬኤለ አብርሃ ከነበረበት ቦታ ቀይሮው በማእከላዊ ዞን ዋና
አስተዳዳሪ ሲያደርጉት። አቶ አዳነ አሰፋ ደግሞ ይሰራበት ከነበረ ቦታ በማግለል ከስራ ውጭ አድርገውት እንዳሉ። ከዞኑ ፅ/ቤት ውስጥ
አፈትልኮ የወጣ ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በስርአቱ ውስጥ የሚገኙ የበላይ አመራሮች በየግዜው የሚያሳዩት ስልጣንን
መነሻ ያደረገ ልዩነትና በጥላቻ የመተያየት ሁኔታ። በባሰ መልኩ እየቀጠለ መሆኑ በተለያየ ግዜ መግለፃችን ይታወቃል፣