Tuesday, December 3, 2013

የኢህኣዴግ ስርኣት እየተከተለው ባለው ፀረ ህዝብ አሰራር። መላው ያገራችን ህዝብ በስርኣቱ ያለው አመኔታ ክፉኛ በመውረዱ። ጭንቀት የወለደው እርምጃ በመውሰድ መጠመዱን ተገለፀ፣



በምእራብ ትግራይ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ አካባቢዎች በሚገኙ። በማይ ካድራ፤ በረከትና ሑመራ። ከሞተር ሳይክል ጀምሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ይዞው ለሚንቀሳቀሱ የቀን ሰራተኞችና የኣካባቢ ነዋርወች። በየመንገዱ በተሰማሩ የፀጥታና የመከላከያ ሃይሎች እየታገቱ። መታወቅያና ማንጃ ፍቓድ እንዲያሳዩ በማስገደድና በመፈተሽ። ከእለታዊ ስራቸው እንዲተጓጎሉና ጭንቀት ውስጥ እዲገቡ እየተደረገ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
     ያካባቢው የፀጥታ ሃይሎች። መታወቅያ ካርድ እየጠየቅናቸው ነን የሚል ሽፋን በመጠቀም። ተሽከርካሪዎቹ በየመንገዱ እንዲቆሙ በማድረግ ገንዘብ እንደሚቀበሉና እንደዚሁም ያለ ምንም ፍቃድ አስገድደው ከተጫነው ጭነት የተለያዩ ንብረት እንደሚወስዱ ያመለከተው ይሀው መረጃ።
በተለይ ከፍተሻው ብኅላ የመታወቅያ ካርዱን ለግዜው በእጁ ያልያዘ ወገን ትታሰራለህ በሚል የማስፈራርያ ቃል ተጠቅመው። ብዛት ያለው ገንዘብ በጉቦ መልክ እየተቀበሉ እንዳሉና። ገንዘብ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ለቀሩትም። ከበላይ አለቆቻቸው ተመካክሮው እንዲታሰሩ በማድረግ። ከዚህ ተምሮው ሌሎቹ ጉበውን እንዲሰጡ እየተጠቀሙበት ነው ሲል። በላያቸው ላይ በደሉ ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን መሰረት ያደረገ መረጃ ኣስረድተዋል፣