Friday, December 6, 2013

በምእራብ ጎጃም አዊ ዞን የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ከመጠን በላይ በሆነ መዋጮ ኑሮአችንን መምራት አልቻልነም ሲሉ ቅሬታቸዉን እያሰሙ እንደሆኑ ከቦታዉ የደረሰን መረጃ ያስረዳል፣




እነዚህ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ጉልበታችንንና እዉቀታችንን ያፈሰስንበትን የወር ደሞዛችንን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ለተለያዩ መዋጮዎች እንድንከፍል እያስገደደን ስለሆነ። በዚህ ላይ የኑሮ ዉድነት ተጨምሮበት ቤተሰቦቻችንን ልናስተዳደር አልቻልነም ሲሉ በምሬት ገለጹ፣
   መርጃዉ! ለችግሩ ሰለባ የሆኑትን ዋቢ በማድረግ። በስልጣን ላይ የሚገኘዉ ስርዓት ለመዋጮ እያለ የሚያነሳቸዉና የሚፈጥራቸዉ ቁጥር የላቸዉም በማለት። በተለይም ደግሞ ባላ-መንበት የአባይ ግድብ፤ ለስፖረት፤ ለግብርና ሌላም ሌላም እየተባለ ግማሽ የሚሆነዉ ደመወዛችን ይቆረጥብናል ካሉ በኋላ። በዚ ምክንያት ደግሞ ከእጅ ወደ አፍ የነበረዉ ኑሮኣችንን አባብሶት ወደከፋ ሂወት ወድቀናል በማለት ምሬታችውን ኣሰሙ፣
     የኢህአዴግ ባልስልጣናት። የመንግስት ሰራተኛዉ እየከፈለ ያለዉ መዋጮ በፍላጎቱ ካልሆነ በስተቀር የሚያስገድዳቸዉ አካል የለም ኣያሉ በሚድያ የሚናገሩት ከሓቅ የራቀ የፖለቲካ ፍጆታ መሆኑን የችግሩ ሰለባ የሆኑ ዜጎች አክለዉ አስረዱ።
     ከዞኑ ሳንወጣ በመንግስት ስር ተመድበዉ በአንድ አይነት ሞያ እየሰሩ ያሉ የጤና ኤክስቴሽን ሰራተኞች። በደመወዝ አከፋፈል ላይ አይኑን ያወጣ አድልዎ እየተፈፀመ ነዉ ካሉ በኋላ። የኢህአዴግ ካድሬዎችና አሽከሮቹ 1,428ብር ሲከፈላቸው። አባልና ደጋፊ ላልሆኑ ደግሞ 928 ብር ብቻ ኣየተከፈላቸዉ ኣንዳለ ምንጮች ከቦታዉ ግለፁ፣
     መረጃዉ ጨምሮ እንድሚያስረዳው። እነዚህ በአንድ አይነት ስራ ተሰማርተው ተመሳሳይ  የአግልግሎት ግዜ ያላቸው የጤና ኤክስቴሽን ሰራተኞች እየተፈጸመ ነው ያሉት አድልዎ። ለሚመለከታቸዉ አካላት ጥያቄአቸዉን ቢያቀርቡም። ደመወዛችሁ እንዲጨመርና ሌሎችንም ጥቅማቅሞች ልታገኙ ከፈለጋችሁ የኢህአዴግ አባል መሆናችሁን አረጋግጡልን የሚል መልስ እንደሰጥዋቸው ለማወቅ ተችልዋል፣
      በአሁኑ ግዜ የደመወዝ ጭማሪ፤ የተለያዩ ጥቅማጥቅምና  የስልጣን ቦታ የሚሰጣቸዉ ሰራተኞች። በሞያቸዉና በአቅማቸው ታይተው ሳይሆን። የኢህአዴ አባል በመሆናቸዉና ባለመሆናቸው እየተመዘኑ ብቻ እንደሆነ መረጃዉ አክሎ ያስረዳል።