Friday, December 6, 2013

ባልፈዉ ሳምንት በመቀሌ ከተማ ዉስጥ የሚግኙ ከ 1000 በላይ የሚሆኑ የንግድ ድርጅቶች ሕገ ወጥ በሆነ ኣሰራር እንዲታሸጉ እንደተደረገ የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣



በመረጃው መሰረት ይህ በስልጣን ላይ ያለው ስርኣት እየተከተለው ባለው የንግድ ኣሰራር ሂደት። በመቀሌ ከተማ በህጋዊ መንገድ ብንግድ የስራ ዘርፍ ተሰማርተዉ የሚገኙ ባለሃብቶች ነጋ ጠባ በሚቀያየር። ሃላፊነት የጎደለዉ አሰራር ዕለታዊ ስራቸዉን በሰላም እንዳያከናዉኑ በስርዓቱ ካድሬዎች ተሰናክለዉ የቆዩ ሲሆን። አሁንም ፋክቱርና ሌሎች ምክንያቶችን እየፈጠሩ ካለፈዉ በከፋ መልኩ ሆን ብለው። ሥራቸዉን እንዳይሰሩ እንቅፋት እየፈጠሩባቸዉ መሆኑን በችግሩ ሰልባ ከሆኑት ነጋዴዎች  የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
        ይህ ከትግራይ ክልል ዉጭ በሌሎች ክልሎች ያልተሰራበት አዲስ ህገ-ወጥ አሰራር። ማነኛዉም ነጋዴ በየቀኑ የገዛበትንና የሽጠበትን ፋክቱር መያዝ አለበት ይሚል ሁኖ፣ ይሀ አይነት አሰራር ከተሰጠ አንድ ወር እንኳን ሳይሞላዉ በንግዱ ዘርፍ  ለተሰማሩ ዜጎች ችግር ዉስጥ እንዳስገባቸዉና። ይህ በመቀሌ  ከተማ ብቻ ተግባር ላይ እንዲዉል ታስቦ የተደረገ በመሆኑ በዚህ ሳምንት ብቻ ከአንድ ሽህ 1000 በላይ የንግድ ተቋማት እንደታሽጉና። የከፋዉ ደግሞ በከተማዋ ዉስጥ በተለምዶ ቀዳማይ ወያኔ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢብቻ ከሁለት መቶ በላይ የንግድ ድርጅቶች በመታሽጋቸዉ። ነጋዴዎቹ እየደረሳባቸዉ ባለዉ። ፍትሓዊነት የጎደለዉ አሰራር እያማረሩ መሆናቸዉን ለማዎቅ ተችልዋል፣