Sunday, December 8, 2013

በአማራ ክልል ኣዊ ዞን የዳንግላ ነዋሪዎች በወረዳው ባለስልጣናት ከመኖርያ ቤታቸው እየተፈናቀሉ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ከኣካባቢው ገልጠዋል፣




በደረሰን መረጃ መሰረት የወረዳ ዳንግላ ነዋሪዎች ከሁለት አመት በፊት መሬት ገዝተው ቤት ሰርተው ይነሩበት ከነበሩ መኖርያ ቤታቸው የስርአቱ ባለ ስልጣናት ቅድመ ዝግጅነት እና ካሳ ሳይሰጣቸው ከህዳር 18/ 2006 ዓ.ም ጀምረው እያፈረሱ ስለ ሚገኙ በርከት ያሉ ሽማግሌዎች እና ህፃናት የሚገኝባቸው ዜጎቻችን ለፀሃይ እና ንፋስ እንዲሁም ለህመም እና ሞት ተጋልጠው እንደሚገኙ አስረድተዋል፣
   በተጨማሪ ነዋሪዎቹ ለደረሰባቸው ድንገተኛ የቤት ማፍረስ የዝግጅት ቀን እንዲሰጣቸው እንዲሁም ላወጡት ወጪ ካሳና ተለዋጭ መሬት እንዲሰጣቸው ወደ ሚመለከታቸው ኣካላት ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ ኣካል በማጣታቸው በበረሃ ተጥለው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ታወቀ፣
   ይህ ህጋዉነት የጎደለው የህዝብ ቤቶች የማፍረስ ተግባር በመላው አገራችን እየተፈጸመ መሆኑ የጠቆሙ  ይህ ደግሞ ለወያኔ ኢህኣዴግ ባለስልጣናት ወደ ኪሳቸው የሚገባ ገንዘብ ካልሆነ በስተቅር ለህዝብ የማይቆረቆሩ ጨካኞች  መሆናቸውን የሚያሳይ ተግባራቸው ነው ሲሉ ታዛቢዎቹ ጨምረው ኣስረድተዋል፣