Sunday, December 8, 2013

የወረዳ ፀገዴ ዳንሻ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ፍትህ በአድልዎ ሁነዋል ሲል ህዳር 24/ 2006 ዓ,ም በስርአቱ ላይ የተቃዉሞ ሰልፍ እንዳደረገ ተገለፀ፣




በደረሰን  መረጃ መሰረት/ በትግራይ ምእራባዊ ዞን ዳንሻ ከተማ ህዳር 24/ 2006 ዓ.ም የተካሄደዉ ሰልፍ ያስተባበሩት እና የመሩት ሻለቃ ኣብርሃ ገብረዝጊኣብሄር የተባሉና  የቀድሞ የህወህት ተጋዮች እንደሚገኙባቸው ታውቋል፣
    ታጋዮቹ በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጓዶቻችን ለፍትሕ እና እኩልነት ሲሉ ተሰዉተዋል እኛም ደግሞ የወያኔን ክህደት እዩ ሲለን ለተመሳሳይ አላማ ግማሽ አካላችን ካጣን በኋላ በዳንሻ በበረሃ ተጥለን እነገኛለን ብለዋል፣
  ታጋዮቹ ኣያይዘዉ በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ህግና ኣሰራር መሰረት ያደረገ ሳይሆን ሁሉ ስራው በኣድልዎ እና በጥቅም የተያያዘ በመሆኑ ሓቅ እና ፍትህ በገንዘብ ተረግጧል በማለት ህዝቡን ኣነሳስትው እንዳሰለፉት ምንጮቻችን ከላኩልን መረጃ ለማወቅ ተችለዋል፣
   ይህ ከ1500 ሰዎች በላይ የተገኙበት የተቃዉሞ ሰልፍ ለመነሳሳት ዋነኛው ምክንያት አለቃ ካህሳይ የተባለ የስርአቱ አባል የዳንሻ ከተማ ነዋሪ  ለሆነችው ወ/ሮ ስላስ ለተባለች ሚስቱ እኔ ብሌለሁበት የግብር ወረቀት ለምን ትቀበያለሽ በሚል ምክንያት ቤት ዘግቶ በሚዘገንን ግፍ እጃዋ እና እግራዋን ቆራርጠዋል  በሚል መሆኑን ታውቋል፣
   ወንጀለኛው በፖሊስ እየተጣራ እያለ በቤተሰቡ በኩል ለዳኛ፤ ለአቃቤ ሕግ፤ እና ለመርማሪ ፖለስ  ከ30 ሺ ብር በላይ ጉቦ በመክፈል ለተከሰሰበት ከባድ ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርቦ ህጋዊ ዉሳኔ እንዳያገኝ ባካሄዱት ጥረት 6 ዓመት ብቻ እንዲታሰር በመወሰኑ። ይህ በገንዘብ ሓይል የተሰጠ የተዛባ ዉሳኔ እስካልተስተካከለ ድረስ ተቃዉሞው ተጠናክሮ እነደሚቀጥል የዳንሻ ከተማ ነዎሪዎች  አስታውቀዋል፣


ከዞኑ ሳንወጣ በፀገዴ ወረዳ  የሚገኙ ፖሊስ በሳሮቋ ቀበሌ አንድ ሽፍታ ከሌሎች አስር ግብረአበሮቹ  ለማደን ብለው ህዳር 16 /2006 ዓ.ም ባካሄዱት ዘመቻ ሙትና ቁሱል መሆናቸው ተገልጠዋል፣
    በመረጃው መሰረት በትግራይ ምእራባዊ ዞን ወረዳ ፀገዴ ሰሮቋ ቀበሌ  ሽፍታ ለማደን ብለው ህዳር 16 /2006 ዓ.ም የተሰማሩ ሁለት ፖሊስ የሚገኙባቸው 6 የምልሻ ኣባላት፣ በስርኣቱ ተማርሮ የወጣ ሽፍታ ከኣጋሮቹ ጋር በመሆን  ለቆሰሉት 2 ፖሊስ እና 3 ሚልሻ የአካባቢው ወጣቶች ኣስተባብሮ በማንሳት ለአካባቢው ነዋሪ ሕብረተሰብ ሰብስቦ ብህዝብ ላይ በደል ሲፈፅሙ የቆዩ  እነዚህ ናቸው እንጂ እኛ አይደለንም ብሎ በማስረዳት፣ ለረዳት ኢንስፔክተር ዋሻው ከበደና ለዋና ሳጅን ጌታቸው ኤፍሬም ወድያዉኑ ሲረሽናቸው ለቆሰሉት ሚልሻ  ተስፋየ ማትዮስ፤ አሕመድ ከድር እና አሳየሀኝ ተጫነው ለተባሉት ደግሞ ግዝያዊ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ በማድረግ ምክር ሰጥቶ ነፃ እንደለቀቃቸው  ከደረሰን መረጃው ለማወቅ ተችለዋል፣