Tuesday, April 8, 2014

ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ዛግር ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ለህዝብ ተብሎ የመጣውን እህል ለግል ጥቅማቸው እንዳደርጉት ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አስታውቀ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታሕታይ አድያቦ ወረዳ የዛግር ቀበሌ ወረዳዎች እለታዊ ችግራቸውን ለመፍታት ሲሉ በሴፍትኔት መልክ የመጣላቸውን እህል የወረዳዋ አስተዳዳሪዎች ሽጠው ለግላቸው እንዳደረጉት የገለፀው ይህው መረጃ ለዚህ እኩይ ተግባር ዋነኛ ተዋናኝ የሆነው ደግሞ የዛግር ቀበሌ አስተዳዳሪ አብረሃ ገብረዝግሄር እንደሆነ ለማወቅ ተችልዋል።
    የዛግር ቀበሌ አስተዳደር ህዝቡ ደክሞ የሰራበትን እህል በወቅቱ ለህዝቡ ከማከፈፍል ይልቅ ዛሬ አንሰጣችሁም ነገ መጥታጣችሁ ውሰዱ በማለት ካባረራቸው በኋላ በመጋቢት 11/2006 ዓ/ም ለሊት 90 ኩንታል ስንዴ ለነጋዴዎች በመሽጥ ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው የተገኘው መረጃ አስረድትዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዛግር ቀበሌ ነዋሪዎች ያለባቸውን የአንቡላንስ ችግር በመንግስት ሊፈታ ባለመቻሉ ይህንን ለመፍታት ተብሎ አንድ ቤተሰብ በአመት 10 ብር እንዲያዋጣ በወረዳ ደረጃ ትእዛዝ የወረደ ሲሆን የቀበሌዋ አስተዳደር ግን 20 ብር ለአንድ ቤተሰብ እያስከፈለ የቀረውን ገንዘብ ስላጠፋፋው ነዋሪው ህዝብ በበኩሉ ያዋጣነው ገንዘብ ይመለስልን ብለው ለሚመለካታቸው አካላት አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም የሚሰማቸው ባለስልጣን እንዳላገኙ ለማወቅ ተችልዋል።