በመረጃው መሰረት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
ባለ ስልጣናት ከህዝቡ ሊያጋጥማቸው የሚችል ተቃውሞ በመሳርያ ሃይል ለመጨፍለቅና የስልጣን ግዝያቸውን ለማራዘም ብለው በርከት ያሉ
ወጣቶች መልምለው ብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ውስጥ ለማስገባት ያሰቡትን እቅድ በኢትዮጵያ ህዝብ ተቃውሞ እያጋጠማቸው ባለበት ባሁኑ ግዜ
እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ከ8ኛ ክፍል በላይ ለሆኑ ወጣቶች መቀሌ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ያካባቢ መስተዳድሮች እያንዳዳቸው
1,600 ወጣት መልምለው እንዲያቀርቡ ጥብቅ ትእዛዝ ቢሰጣቸውም ለቀረበላቸው ትእዛዝ በመቃወም ወጣቶቹ ወደ አ/አበባና ሌሎች ያገራችን
ከተሞች እየሸሹ መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።
ያካባቢ መስተዳድሮቹ ወጣቶቹን ወደ ውትድርና ለመመልመል ለተሰጣቸው መመርያ
ከህዝቡ ተቃውሞ ስላጋጠማቸው 10ኛ ክፍል ጨርሰው ስራ ላጡና የጎዳና ተዳዳሪዎች ለሆኑ ወጣቶች በመሰብሰብ ስራ
እንፈጥርላቹሃለን ተመዝገቡ ብለው በማታለል ወደ ወትድርና ለማስገባት ሞክሮው ሊሳካላቸው እንዳልቻለ መረጃው አክሎ አስረድተዋል።