Wednesday, April 9, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ስለመሬት አጠቃቀም በሚል የተካሄደው ስብሰባ ያለ ፍሬ እንደተበተነ ምንጮቻችን ከሑመራ ከተማ ገለፁ።




በዞኑ ያለውን የመሬት አጠቃቀም በሚመለከት በሑመራና በፀገዴ መጋቢት 15 /2006 ዓ.ም ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ለዚህ መድረክ ይመሩት የነበሩ ባለስልጣናት ህዝቡ በመሬት አጠቃቀም ላይ ችግር እንዳለበት አስመስለው በስብሰባው መክፈቻ ላይ ለማቅረብ በሞኮሩበት ግዜ የስብሰባው ተካፋይ ወገኖች በበኩላቸው በመሬት አጠቃቀም ላይ ችግር እየፈጠረ ያለው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት መሆኑን በማስረጃ አስድግፈው እንዳቀረቡ የስብሰባው ተሳታፊዎችን መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
    በተጨማሪ የስብሰባው ተካፋዮች አንድ በአንድ እንደተናገሩት መሬት ህጋዊነት ባልተላበሰ መንገድ እየተሸጠና በጉቦ እንዲሰጥ እያደረገ ያለው መንግስት እራሱ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚያውቀው ሃቅ ነው፤ እየተከተላችሁት ያለው ብልሹ አስራር ደግሞ ክራይ ሰብሳቢነትን ከግዜ ወደ ግዜ እያስፋፋ የመሬት አስተዳደሩን አበላሽቶታል በማለት ተሰብሳቢዎቹ በምሬት እንደተናገሩ  ለማወቅ ተችልዋል።
       በተለይ በሑመራ ከተማ ውስጥ የነበሩ የስብሰባው ተካፋዮች መንግስት በሁሉም ቦታዎች እየተከተለው ያለው ብልሹ የሆነ  የአስተዳደር ሁኔታ ከስር መሰረቱ ከማሰውገድ ይልቅ ህዝቡ ላይ ችግር እንደደረሰ አስመስሎ መቅረብ ሁለተኛ በደል መሆኑን መግለፃቸውና ይህንን የህዝቡን ምሬት ደግሞ ስብሰባውን ይመሩት የነበሩ አካላት ስላልተቀበሉት ተሰብሳቢዎች በነዚህ ባለስልጣናት መልስ ተበሳጭተው ስብሰባው ረግጠው እንደ ተበትኑ፤ በፀገዴ የነበሩት ተሰብሳቢዎችም ያለምንም መግባባት እስከ መጋቢት 16/2006 ዓ.ም በስብሰባ ተጠምደው እንደሰነበቱ የደረሰን መረጃ አመልክትዋል።