እነዚህ በሽሬ ከተማ
ውስጥ ማይ ድሙ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ሃያ በሃያ (20 በ 20) በሚል ለመኖርያ ቤት መስርያ የሚሆን መሬት ተሰጥቶዋቸው ያስገነቡት
ቤት የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ባወረዱት ትእዛዝ መሰረት አፍራሽ ግብረ-ሃይል በማሰማራት 12 የመኖርያ ቤቶች እንዳፈረሱ ተበዳዮቹን
መሰረት በማድረግ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ መኖርያ ቤታቸው የፈረሰባቸው ንፁሃን ዜጎች
ያለምንም መጠለያ አውላላ ሜዳ ላይ ተጥለው ለንፋስና ለጸሃይ በመጋለጣቸው ምክንያት በላያቸው ላይ ተፈፅሞ ላለው ጸረ ህዝብ ድርጊት
መፍትሄ እንዲደረግላቸው ወደ ሚመለከታቸው አካላት ጥሪያቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ አካል እንዳላገኙ የተገኘው መረጃ ገልፀዋል።
ስርአቱ
በሚያሰማራቸው የመኖርያ ቤት አፍራሽ ግብረ ሃይል በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች እየተፈፀመ ያለው ፀረ ህዝብ ድርጊት የዜጎችን ሰብአዊ
መብት ጥሰት እንደሆነ በተለያዩ ግዝያት በዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።