እነዚህ 70 የሚሆኑ
ወርቅ በማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩ ወገኖች የትጥቅ ትግል ለሚያካሂዱ ተቃዋሚዎች ትተባበራላቹህ ተብሎው በአካባቢው
በሚገኙ ፌደራል ፖሊስ ተይዘው እንደተወሰዱና ምንም የፈፀሙት ወንጀል ሳይኖር ወደ ሽሬ፤ ማይ ገባና፤ ሁመራ ከተማ ወስደው እንዳሰርዋቸው
ለማወቅ ተችለዋል።
እስር ቤት ውስጥ ታስረው ካሉ ንፁሃን ዜጎች ውስጥ አቶ ዛጌ፤ አቶ ሻምበል
አቶ ፍስሃና አቶ አጥናፉ የተባሉ እንደሚገኙባቸውና ለወርቅ መመርመርያ አገልግሎት የሚውል ለአንድ ማሽን በ185 ሺ ብር ሂሳብ የገዙትንና
ጠቅላላ 45 ቱግኒስቱና ዲቬክስ የተባሉ ማሽኖች እንደተወረሰባቸው መረጃው አክሎ አስታውቀዋል።