Saturday, May 31, 2014

የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት የክፍለጦር አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በመጪው ዓመት 2007 ዓ/ም እንዲካሄድ በታሰበው አስመሳይ ምርጫ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ሃይሉ ከጎናቸው እንዲቆም በማለት በጥቅም አታልለው በቁጥጥራቸው ውስጥ ለማስገባት ላይና ታች እያሉ መሆናቸው ታወቀ።



የክፍለጦር አዛዦች በየግዜው ከሰራዊቱ የሚነሳውን የስንብት ጥያቄና ሌሎች የመብት ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ስልጣናቸው በመጪው የ2007 ዓ/ም ምርጫ ላይ እንዳይነጠቅ በመስጋት ሰራዊቱን በመሰብሰብ ለእያንዳንዱ መኖርያ ቤት እንደሚሰራለትና ኣስከባሪ ሃይል ከተገኘ ገንዘብ 25% የሚሆነውን   በባንክ እናስቀምጣለን በማለት ተግባር ላይ የማይውሉ ቃል ቢደረድሩም ተሰናብታችኋል ተብለው የተለዩትንና የስንብት ደብዳቤያቸውን እየተጠባበቁ ያሉት የበላይ መኮንኖች የሚገኙባቸው ወታደሮች ግን ሃሳቡን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል።
     ለስንብት ተለይተው የመሰናበቻ ደብዳቤ እየጠበቁ ከነበሩ የበላይ አመራሮች እንዳንዶቹን ለመጥቀስ-
ኮሎኔል ፀጋይ ግርማይ የፖለቲካ ምክትል ሃላፊ
ኮሎኔል ዓፈራ በሰሜን እዝ የጀኔራል ሰዓረ መኮነን አማካሪ የነበረና
ኮሎኔል ንጉሰ ( ወዲ ጨርቆስ ) የ11 ክፍለጦር አዛዥ ሲሆኑ
አሁንም በስራ ላይ ያሉትና ለስንብት ከተዘጋጁት የ 21 ክፍለጦር አዛዦች ደግሞ-
ሻለቃ አደራጀው ተክሉ የረጅመንት ፖለቲካ አዛዥ
ሻለቃ ሸጋው አለሙ የረጅመንት ምክትል አዛዥ
ሻለቃ ጉዕሽ የረጅመንት ምክትል አዛዥ
ሻለቃ ፀጋይ የረጅመንት ምክትል አዛዥና
ሻምበል ቀድሬላ የክፍለጦር የስለያ ሃላፊ ናቸው።
  ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንኛውም ወታደር ፍቃድ ከተሰጠው ጊዜ ጀምሮ 10 ቀን አሳልፎ ወደ ክፍሉ የተመለሰ አባል እንደ አንድ ወንጀለኛ ታይቶ ያለ ምንም የስንብት ደብዳቤና የገንዘብ ድጋፍ ይባረራል የሚል አዲስ ህግ መውጣቱ ከመከላከያ ሰራዊቱ የተገኘው መረጃ ገልጿል።