Saturday, May 31, 2014

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በምግብ እጥረትና በቂ የትምህርት መሳርያዎች ባለማግኘታቸው ምክንያት በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ትልቅ እንቅፋት እያጋጠማቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በደረሰን መረጃ መሰረት እነዚህ በአድግራት ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች በቂ ምግብ ባለማግኘታቸውና የተገኘውም ቢሆን ደረቀ ዳቦ መሆኑን የገለፀው መረጃው ተማሪዎቹ ላጋጠማቸው ችግር መፍትሄ እንዲደረግላቸው ለዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ለዶክተር ጋይም/ ዛይድ/ ብሶታቸው ቢያቀርቡም ተገቢ መልስ እንዳልሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።
    ይህ በእንዲህ እንዳለ ለሰኔ 25/ 2006 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው እንዲካሄድ የታሰበውን የዓመቱ ማጠቃለያ ፈተና በዩኒቨርሲቲው ውስጥ አጋጥሞ ባለው የምግብና የትምህርት መሳርያዎች እጥረት ምክንያት ተማሪዎቹ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳልቻሉ መግለፃቸውን ለመረዳት ተችሏል።
    እንደሚታወቀው የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ችግር ላይ እንዳሉና ቀደም ሲልም የዩኒቨርሲቲው የበላይ ሃላፊዎች ዶክተር ጋይምና /ዛይድና/ ምክትሉ ዶክተር ዘለአለም በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለው ችግር እንፈታዋለን ማለታቸው  ባለፈው የዜና እወጃችን መገለፁ ይታወቃል።