Friday, May 16, 2014

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በከተማዋ ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት መካከል በተፈጠረ ግጭት፣ 4 ንፁሃን ዜጎቻችን እና 2 የስርዓቱ የፖሊስ አባላት እንደሞቱ ምንጮቻችን አስረዱ፣፣



በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ገንፎ-ቁጭ ወይም ጨረቃ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ፣ በነዋሪዎችና በአካባቢው የፖሊስ አባላት መካከል ግጭት መነሳቱን የገለፀው መረጃው፣ የግጭቱ ጠንቅም የስርዓቱ ተላላኪ በሆኑት ቤቶችን ለማፍረስ በቀለም ምልክት ለማድረግ ሲሞከሩ ህዝቡ ደግሞ “ቤታችን ሲፈርስ ዝም ብለን አናይም’ በማለት በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል፣፣
ቤታችን መፍረስ የለበትም በማለት ተቃውሞ ካነሱት ውስጥ አንድ ሚሊሻ ጨምሮ አራት ንፁሃን ዜጎች ሲሞቱ ህዝብ ለመጨፍጨፍ  ከተላኩት የስርዓቱ የፌድራል ፖሊሶች መካከል 2 ተገድለው አንድ ክላሽ ኮፍ መሳሪያ ደግሞ በህዝብ እንደተማረከ ታውቋል፣፣
   በተመሳሳይ ከባህርዳር ከተማ መኮድ ከተባለው ወታደራዊ ካምፕ በመጡ ብዛት ያላቸው የስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሚያዝያ 26/2006 ዓ/ም ቤት እየፈረሰ በነበረበት ወቅት ቤታችንን አናስፈርስም በማለት የተከላከሉ ዜጎችን በዱላ እየቀጠቀጡ አድራሻው ወደ አልታወቀ ቦታ በሌሊት እንደወሰዷቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣