በመረጃው መሰረት በሁሉም
የመቐለ ከተማ አስተዳድሮች አካባቢ ለሚገኘው ህዝብ የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች ባካሄዱት ስብሰባ ላይ የመወያያ አጀንዳ ሁኖ የቀረበው
“ጠላቶቻችን ሳይመጡብን አካባቢያችንን እንጠብቅ ፀጉረ ልውጥ ካየን ደግሞ ለፖሊስ እናመልክት የሚል ስጋት ያደረባቸው መመሪያዎችን የያዘ አጀንዳ እንደነበረ ለማወቅ ትችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እንደዚህ አይነት ስብሰባ ከተካሄደባቸው የአካባቢ
መስተዳድሮች አንዱ አይደር ሲሆን ስብሰባውን ይመሩ ከነበሩት የህወሃት ኢህአዴግ ተላላኪ ካድሬዎች ውስጥ የአስተዳደር ፀጥታ ሃላፊው
አማኑኤልና ኢንስፔክተር ምሩፅ የተባሉ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው ተሰብሳቢዎች በበኩላቸው ጠላትና ፀጉረ ልውጥ የምትሏቸውን ሰዎች
ንገሩን ትላንት ጠላት የለንም ስትሉን አልነበረም ወይ በማለት በህዝብ የቀረበውን ጠንካራ ጥያቄ የስርዓቱ ተላላኪ ካድሬዎችም በፊናቸው
ግዜው ሲደርስ እንነጋገርበታለን ብለው ሽፋፍነውት እንዳለፉ ታውቋል።