Saturday, May 17, 2014

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን ለሚገኝው፣ ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ መስርያ በማለት ከሚያዝያ 8/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ በአከባቢው ለሚኖሩ ዜጎቻችን በስርዓቱ እየተፈናቀሉ እንዳሉ ታወቀ፣፣



በመረጃው መሰረት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ መተከል ዞን፤ ፓዊ ወረዳ፤ መንደር ዘጠኝ፤ አምስት፤ ስምንትና በሌሎችም አካባቢ ሲኖሩ ከቆዩት ከ 4ሺ በላይ ዜጎቻችን፣ ከመኖሪያ ቤታቸው በሃይል እየተፍናቀሉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው በዚህ የተነሳም ተንከባክቦው ያሳድግዋቸው ቋሚ ተክሎቻቸውና መሬታቸውን ትተዉ መሰረተ ልማት ወደሌለበት ማንቡክ ወረዳ ጃባ በሚባለው በረሃ እንዲሰፍሩ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፣፣
በተመሳሳይ  ለቤንሻንጉል ጉምዝ ተጎራባች የሆኑ የአማራ ክልል አዊ ዞን ከ2500 በላይ በባየሽና ኢላላ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑት ዜጎች በሰልጣን ላይ ያለው ሰርዓት ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሚውል የሸንኮራ አገዳ ማልሚያ በሚል ሽፋን መኖሪያ ቤታቸውን እያፈረሱ የእርሻ መሬታቸውንም እየቀሟቸው ወደ ማንቡክ ወረዳ ጃባ በረሃ ላይ እንዲሰፍሩ ስላደረጓቸው  ለተለያዩ በሽታዎችና ለሞት ተዳርገው እንዳሉ መረጃው አክሎ አስረድቷል፣፣