በአማራ ክልል የጎንደር
ከተማ ነዋሪዎች በስርዓቱ ተላላኪ አስተዳዳሪዎች መሬታቸውን ያለምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት እየተነጠቁ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው
በዚህ የተነሳም ነዋሪዎቹ በላያቸው ላይ እየተፈፀመ ያለውን የሰባአዊ መብት ጥሰት እንዲገታ በማለት። ግንቦት 1/2006/ዓ,ም ሰፊ
ተቃውሞ ማካሄዳቸው ከከተማዋ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
በህዝቡ ተቃውሞ የሰጉ የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው በከተማዋ የፌዴራል
ፖሊስ በማሰማራት መብታችን ይከበር እያለ ድምፁን በተቃውሞ ሲያሰማ ለነበረው ህብረተሰብ መሳርያ ተጠቅመው እንዲበተን ቢያድርጉትም ነዋሪዎቹ ግን በፖሊሶቹ ድብደባና ማስፈራርያ ሳይገቱ አንድነት በመፍጠር ወደዞን
አስተዳደሩ በመሄድ አቤቱታቸውን እንዳቀረቡ ታውቀዋል።
ነዋሪዎቹ ወደ ዞኑ አስተዳደር በመሄድ ሲያሰሟቸው ከነበሩ አቤቱታዎችም
መሬታችንን መንግስት በሊዝ እየሽጠው ነው። እኛ ግን መኖርያ አጥተን በከባድ ችግር ላይ ወድቀን እንገኛለን መብታችን ተርግጧል!
ሃሳባችንን እንዳንገልፅና ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናደርግ ተከልክለናል የሚሉና ሌሎችንም ያቀረቡ ቢሆኑም የሚሰማቸው አካል እንዳላገኙና
በዚህም ምክንያት የተናደዱ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥያቄአቸው እስኪመለስ የማያቋርጥ ተቃውሞ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የደረሰን
መረጃ አክሎ አስረድቷል።