በትግራይ ምዕራባዊ ዞን
እየተካሄደ ያለው አዲሱ የመሬት ክፍፍል ህዝብ እንዳልተቀበለውና የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንዳለ የገለፀው መረጃው
በዚህ የሰጉ የስርአቱ ካድሬዎች ደግሞ በሁሉም ወረዳዎች ለሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች በሑመራ ከተማ እንዳተጠምቀ በሚባለው አዳራሽ
በመሰብሰብ ህዝብ ተቃውሞ እንዳያደርግ እንዲገዝቱላቸው መምሪያ እንደስጧቸው ለማወቅ ተችሏል።
እነኚህ በወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች ትእዛዝ የተሰበሰቡ የሃይማኖት
መሪዎች ህዝቡ አዲሱን የመሬት ክፍፍል አስመልክቶ ግርግር እንዳያነሳ በነፍስ አባት የያዝዋቸው ነዋሪዎች ረብሻና ተቃውሞ እንዳያነሱ
እንዲገዝቷቸውና በመንግስት ላይ ተቃውሞ ማካሄድ በሃይማኖት ክልክል ነው ብለው እንዲያሳምኑ መምርያ ቢሰጣቸውም ከተሰብሳቢ የሃይማኖት
ኣባቶች አንዱ አባ ገብረኪዳን የተባሉት የነፍስ አባት እንድንደግፋችሁ ትክክለኛ ስራ ሰሩ ሲሉ መምሪያዉን እንደተቃወሙት መረጃው አክሎ ኣስረድተዋል።