Friday, May 23, 2014

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ለስርዓቱ ፀረ ናቸው ብለው የጠረጠሯቸውን መኮነኖች ደብዳቤ እየላኩ ከስራቸው እያስቆሟቸው እንዳሉ ታወቀ።




ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አፈትልኮ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በኢትዮጵያ የመከላከያ ስራዊት ውስጥ በከፍተኛ አመራሮችና በጀኔራሎች መካከል አጋጥሞ ባለው አለመረዳዳት የተነሳ ለማይፈልጓቸውና ለስርዓቱ ፀረ ናቸው ብለው ለጠረጠሯቸው የሰራዊት መኮነኖች ደብዳቤ እያላኩ ከስራቸው እንዲቆሙ እያስደረጓችው እንዳሉና የተፈጥረውንም አለምስማማት ለመፍታታ ሲባል የስርዓቱ ተላላኪ የሆኑ የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮነኖቹ በአዲስ አበባ ከተማ በጠንካራ ስብሰባ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከመረጃው ለመራዳት ተችሏል።
   በመጨረሻ መረጃው እንደሚያስረዳው በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ከላይ እስከ ታች  ተፈጠሮ ባለው  የተበላሸ አስተዳድራዊ ጉዳይ ቁጥራቸው የማይናቅ የሰራዊት አባላት እግራቸው ወደ አመራው እየጠፉ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ከዚህ የውትድርና ህይወት በፍላጎታቸው አሰናብቱን እያሉ እንዳሉና አንዳንዶቹ ደግሞ ራሱ ስርዓቱ ለህልውናዬን ያሰጉኛል በሚል ጥርጣሬ እያባረራቸው እንደሚገኝ ሊታወቅ ተችሏል።