Friday, May 23, 2014

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚኖረው ህዝባችን በወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ማዳበርያ እንዲወስዱ በመገደድ ላይ እንዳሉ ታወቀ።



በመረጃው መሰረት መረብ ለኸ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች አዲ ፍታው፤ አዲ በርበሬ፤ ሃፍተማርያምና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖረ ህዝባችን ያለፍላጎቱ የወያኔ ኢህአዴግ ስርዓት አመራሮች ማዳበርያ ውሰድ እያሉ እያስገደዱት እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።
ማዳበርያ አንወስድም ላሉት ዜጎቻችንም እንደተቃዋሚ ተቆጥረው ከባድ በደል እየደርሰባቸው እንደሚገኙ ታውቋል።
  መተጨማሪም የእርሻ መሬት ይኑራቸው አይኑራቸው ማነኛውም በቀበሌዎቹ የሚገኙ አርሶ አደሮች አንድ ኩንታል ማዳበርያ መውሰድ ግዴታቸው እንደሆነ ከገለጹ በኋላ አርሶ አደሮቹ በስርዓቱ አመራሮች እየተፈፀመ ያለው ሃላፊነት የጎደልው ተግባር መፍትሄ እንዲደረግለት ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆኑም ሰሚ አካል እንዳላገኙ ሊታወቅ ተችሏል።
  በተመሳሳይ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ታህታይ አድያቦ ወረዳ የዕጉብ ኬላ ነዋሪ ማህበረሰብ ያለፍላጎቱ በስርዓቱ ካድሬዎች ማዳበርያ ውሰዱ እየተባሉ እንዳሉና አንወስድም ላሉት ደግሞ ብድር እርዳታና ሌላም ሌላም ጥቅማጥቅም አይሰጣችሁም እየተባሉ በስርዓቱ ወሮበላ ካድሬዎች ማስፈራርያ እየተሰጣቸው እንዳሉ የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።