Thursday, May 15, 2014

በአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ችግር የተነሳ በሃገራችን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ በትግራይ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችም እንደተዛመተ ታወቀ።



መረጃው እንዳመለከተው በአዲስ አበባ እየታየ ካለው የዜጎች መፈናቀል የተነሳ ህዝቡ ለዚህ በመቃወም ባካሄደው የተቃውሞ ሰለማዊ ሰልፍ በርከት ያሉ ወገኖቻችን በስርዓቱ ታጣቂዎች ህይወታቸውን እንዳጡ የሚታወቅ ሲሆን በቅርብ ግዜ ደግሞ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ዓዲ ግራት፤ አክሱምና  በሽሬ የእርሻ ማሰልጠኛ ኮለጅ ከባድ ውጥረት ተፈጥሮ እንዳለ ተገለፀ።
   መረጃው በማስከተል በተለይም በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ተቃውሞ ለማሰማት ስልፍ ወጥተው እንደነበሩና በፌደራል ፖሊስ እንደተበተኑ በመግለፅ ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ በሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቹ አድማ ሊያነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት  ከሚያዝያ 26/2006 ዓ/ም ጀምሮ በስርዓቱ የፖሊስ አባላትና የፀጥታ ሃይሎች እየተጠበቁ እንዳሉ መረጃው አክሎ አስረድቷል።