Thursday, May 15, 2014

በከምባታ ዞን አላባ ጠንባሮ ወረዳ ቃጬቢራ በተባለው አካባቢ ለሚገኙ አስተማሪዎች ሚያዝያ 2006 ዓ/ም ለአባይ ግድብ የሚውል ገንዘብ እንዲከፍሉ ተብሎ የተደረገላቸውን ስብሰባ ረግጠውት እንደወጡ ከአካባቢው የተገኘ መረጃ አስታወቀ፣፣



በመረጃው መሰረት በደቡብ ህዝቦች ክልል ከምባታ ዞን አላባ ጠንባሮ ወረዳ ውስጥ፣ የቃጬቢራ የህዝብ ግንኝነት ሃላፊ አቶ ቴድሮስ ጭሌቦ በመራው ስብሰባ ላይ ከራሴ ጀምሮ ሁላችንም ለአባይ ግድብ የሚውል ገንዘብ ከደመዛችን መክፈል አለብን ብሎ ላቀረበው ሃሳብ፣ በተሳታፊዎቹ ተቃውሞ እንደ አጋጠመው ለመረዳት ተችለዋል፣፣
    የወረዳዋ የህዝብ ግንኝነት ሃላፊ በስብሰባው ላይ የወረደውን መመርያ ያልፈፀመ አስተማሪ የወር ደመወዙ ይቆረጥበታል ብሎ ሃይለ ቃል በተሞላበት መንገድ በተናገረበት ወቅት አስተማሪዎቹ ከአዳራሹ ወጥተው  ጥለውት እንደሄዱ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣፣