Thursday, June 19, 2014

ብቃፍታ ሁመራና አካባቢዋ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ከሰኔ 1/2006 ዓ.ም ጀምረው ከመጠን በላይ በሆነ ዋጋ ማዳበርያ እንዲገዙ ስርዓቱ እያስገደዳቸው እንደሚገኝ ታወቀ።



ምንጮቻችን እንደገለፁት የቃፍታ ሁመራና አካባቢው አርሶ አደሮች “የማዳበሪያ ዋጋ በዝቷል ለምንስ ለአንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ2000 ብር እንድንገዛ እንገደዳለን” ብለው ለአስተዳዳሪው በጠየቁበት ጊዜ ለማዳበሪያ 1600 ብር ሲሆን ቀሪው 400 ብር ደግሞ ለአባይ ግድብ ቦንድ መግዣ  የሚውል ነው በማለት ምላሽ እንደሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፣፣
    አርሶ አደሮች ጨምረውም ለምን  እንዲህ አይነት የዋጋ ክፍያ   ይፈፀማል”በማለት ተቃውሞአዊ ጥያቄ ለዋና አስተዳዳሪው ሲያቀርቡ በቀረበላችሁ ዋጋ ትገዙ ከሆነ ግዙ ካልገዛችሁ ግን መሬታችሁን ቀምተን ለሌሎች እንደምናድላቸው ማወቅ አለባችሁ  በማለት የማስፈራሪያ ምላሽ እንደተሰጣቸው ታውቋል፣፣