ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት በስልጣን ላይ ያለው ገዢ መንግስት ህዝብ
ሳይወያይበትና ሳያምንበት 150 ሺህ የሚደርስ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ መታቀፍ አለበት የሚል ትእዛዝ በካድሬዎቹ በኩል ያስተላለፈ
ቢሆንም ህዝቡ ግን የወረደውን ፍትሓዊነት የጎደለውን ትዕዛዝ በመቃዎም ላይ ስለሚገኝ ለዚህ ተቃዉሞ ባጭር ለመቅጨት 150 ሺህ ንፁሃን
ዜጎችን ለተቃውሞ አነሳስታችኋል በሚል ምክንያት በደመነፍስ የከጀላቸውን ዜጎች በነቀምት እስር ቤት ደዴሳ አጉፘቸው እንደምገኝ ታወቀ።
መረጃው ጨምሮ እንደገለፀው በእነዚህ ቀበሌዎች የሚገኝ ህዝብ በስልጣን ላይያለው
ገዢ መንግስት ያወረደውን ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር በመቃወማቸው ምክንያት የታሰሩትን ንፁሃን ዜጎች የሚመለከቱ የተለያዩ አቤቱታዎች
ወደ ስርዓቱ የቀረቡ ቢሆኑም እስካሁን ምንም አይነት መልስ እንዳልተገኘ ለማወቅ ተችሏል።