በማይካድራ
በተካሄደ ህዝባዊ ስብሰባ ገብረፃዲቅ የተባለ የፖሊስ አዛዥ ሶስት ሆቴሎች ህጋዊነት በሌለው መንገድ አሰርቶ ሲጠቀም እንደቆየና ስልጣኑን
ተጠቅሞ ከተገልጋይ ህዝብ በየቀኑ ጉቦ እየተቀበለ ከገቢው ጋር የማይመጣጠን ሃብት ያካበተ መሆኑን ህብረተሰቡ በማስረጃ አስደግፎ
በነበረው ስብሰባ ላይ ያቀረበ ሲሆን ይህንን በሙስና የተጨማለቀ ፖሊስ ግን ለይምሰልና የህዝቡን ቃል ያከበሩ ለማስመሰል ለግዜው
ወስደው እንዳሰሩት ምንጮቻችን አስታወቁ።
መረጃው በማስከተልም ይህ ስነ-ምግባር የጎደለውና በሙስና አይኑ የታወረ የፖሊስ አዛዥ ስልጣኑን ተገን አድርጎ ከሚያገኘው የወር
ገቢው ጋር የማይመጣጠን ሃብት እያካበተ በነበረበት ሰዓት ለምን የሚመለከታቸው አካላት እስካሁን አይተው እንዳላዩ ዝም ብለውት እንደቆዩና
ህዝብ የሰጣቸውን ሃላፊነት ለምን አልተወጡም በማለት እነዚህ አካላት ሁኔታቸው እንዲጣራና የማጣራት ሂደቱም እንደተጨረሰ ውጤቱም ለህዝብ በግልፅ
ይፋ እንዲሆን በነበረው መድረክ ላይ ተሰብሳቢዎቹ እንደጠየቁ ታውቋል።
ይህ አይነት
አስነዋሪ ድርጊት ከዚህ በፊትም በዞኑ የሚገኙ ፖሊሶች በተደጋጋሚ የሚፈፅሙት እኩይ ተግባር እንደሆነና ህዝቡም በየጊዜው ሂስና ግምገማ
እያደረገ ለግዜው የሚታሰሩበት ሁኔታ ቢኖርም እስካሁን በነዚህ ወንጀለኞች ላይ የተወሰደ አስተማሪ እርምጃ እንደሌለ ምንጮቻችን በላኩልን
መረጃ ለማወቅ ተችሏል።