ግንቦት 26 /2006
ዓ/ም የከምሴ አካባቢ ነዋሪዎች ያለ ምንም ድጋፍ በሰፈራ ስም ከነበሩበት ቦታ ተፈናቅለው እንዲሄዱ በመደረጋቸው ምክንያት 3 ሺ
ተፈናቃይ ወገኖች ወደ አካባቢው አውራጎደና (ጥርጊያ መንገድ) በመምጣት በላያቸው ላይ የተፈፀመውን ግፍ በሰላማዊ ሰልፍ እንደገለፁ
ለማወቅ ተችሏል።
ሰፋሪዎቹ ተጥለውበት ካለ አውላላ በረሃ ላይ ወደ አስፋልት መንገድ በመምጣትና
የአበባና ሌሎች ምርት ጭነው የሚያልፉትን ተሽከርካሪዎች በማስቆም በአካባቢው ወደ ሚገኙ ከተሞች ተሳፍረው በመሄድ ብሶታቸውን ለሚመለከታቸው
አካላት ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ እንዳጡና አሁንም በተቃውሞ ላይ እንዳሉ ከቦታው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።