Wednesday, June 4, 2014

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ የሚገኙ ከፍተኛ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊዎች የሃገርንና የህዝብን ገንዘብ እያጠፋፉ መሆናቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን አስረዱ።



በመረጃው መሰረት በወልቃይት ወረዳ በፋይናንስ ቢሮ ጽሕፈት ቤት በህ.ወ.ሓ.ት ማሌሊት ባለስልጣናት ተመርጠው በሓላፊነት የተሾሙ ካድሬዎች በወረዳው በግብርና በቀረጥ እንዲሁም በሌሎች ከህዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው ካዋሉት ግለሰቦች ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ አቶ ኪዳነማሪያም የወረዳው ፋይናንስ ሃላፊ፤ አቶ መኮነን ወልደገርግስ፤ አቶ ይትባረክና ሌሎች ግለሰቦችም እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።
   በተመሳሳይ የቃፍታ ሁመራ ወረዳ አቃቢ ህግ የነበረ መሰረት የተባለ ዜጋ ለብዙ ጊዜ በሙስና ተዘፍቆ ከቆየ በኋላ የሙስና ተግባራት በህዝብ ስለታወቀ ከስራው ቢያግዱትም እስካሁን ተገቢ ፍርድ እንዳልተሰጠው ታውቋል።